እንኳን ወደ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ
ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት
በደህና መጡ!!!

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ይታይሽ ደነቀው መልዕክት

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሴቶች፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አኳያ በዋነኝነት የተሰጡን ተልዕኮ፣ራዕይና አገልግሎቶች ተረባርበን ማስፈጸም ወሳኝ መሆኑ መታወቅ መቻል አለበት፡፡በዋነኝነት በጽ/ቤታችን የምናስፈጽማቸው ተልዕኮዎችበህብረተሰቡ ዘንድ በሴቶች፣በህጻናት፣በአካል ጉዳተኞች፣በአረጋውያንና በስርዓተ ጾታ ጉዳይ ዙሪያ ያለውን የተዛባ አመለካከት መቀየርየማህበራዊ ችግሮችን በመከላከል፣መብትና ደህንነት በማስከበር፣ድጋፍና ክብካቤ አገልግሎት በማስፋት የአካቶ ትግበራን ማረጋገጥህብረተሰቡን በማሳተፍና አደረጃጀቶችን በማጠናከር የሴቶች፣ህጻናት፣አካል ጉዳተኛ፣አረጋውያንና ማህበራዊ ችግር ተጋላጮችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻል ይጠበቅብናል፡፡እንደሚታወቀው በክፍለ ከተማ ደረጃ በቢፒአር ጥናት መሰረት ሁለት(2) አስተባባሪ እና 8 ቡድኖች እንዳሉት ይታወቃል፡፡የነዚህ ቡድኖች ዋነኛ አላማ 18 የአገልግሎት አሰጣጥ በአግባቡ መተግበርና ከላይ ገለጽኳቸውን ዋና ዋና ተልዕኮዎች ማስፈጸም መሆኑ መዘንጋት እንደሌለበት ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡በመሆኑም የጽ/ቤቱን አገልግሎቶች ለማወቅና ግንዛቤ ለማግኘት በዌብሳይታችን አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ
ወ/ሮ ይታይሽ ደነቀው ኃላፊ

ስለ እኛ

about us

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ
ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የማህበራዊ ሲፍቲኔት ኑሮ ማሻሻያ ቡድን
የክፍያ ስርዓት DTO የመተካት ስራ የአገልግሎት አሰጣጥ

Our teams

የ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ  የሴቶች፣ የህጻናት፣ የአካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን መብትና ደህንነት አላምና ራዕይ ለማሳሳካት የሚተጉ ቡድኖቻችን

1. የህፃናት መብት ድጋፍና ክብካቤ ቡድን
2. የማህበራዊ ሴፍቲኔትና ኑሮ ማሻሻያ ቡድን
3. የህፃናት መብት ድጋፍና ክብካቤ ቡድን
4. የማህበራዊ ጥበቃ ቡድን
5. የአካል ጉዳተኛና አረጋዊያን ማስተባበሪያ መከታተያ ቡድን
6. የሴቶች ተጠቃሚነት ቡድን
7. የስርዓተ ፆታ ማካተት ቡድን
8. የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ቡድን

አገልግሎቶቻችን

our services

ማርች 8 ዜና

በማህጸን በር ካንሰር እና በጡት ካሰር ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠር በማድረግ ምርመራ ማድረግ
የቁጠባ ባህል ለማሳደግ በቁጠባ ላይ ግንዛቤ መፍጠር እና ማስቆጠብ
የህዳሴ ቦንድ ግዢ እንዲፈጸም ማድረግ
ለ1 ሳምንት የሚቆይ የባዛር ዝግጅት በማዘጋጀት 15 ኢንተርፕራይዞችን በማሳተፍ ሴቶች ምርቶቻቸውን እንዲሸጡ ተደርጓል
በትምህርት ቤቶች ላይ በማርች 8 በዓል አከባበር ግንዛቤ መፍጠር
ብሮሸሮችን ማሰራጨት
ከተማው ባዘጋጀው የማስ ስፖርት ላይ ሴቶች እንዲሳተፉ ማድረግ

የነጭ ሪቫን ቀን የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው በሚል መሪ ቃል ተከበረ::

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ባዘጋጀው መድረክ”የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው፣ዝም አልልም”በሚል መሪ ቃል የነጭ ሪቫን ቀን በአለም ለ33ኛ ጊዜ በሀግራችን ደግሞ ለ 19ኛ ጊዜ በርካታ የክፍለ ከተማው ሴቶች የክፍለ ከተማና የወረዳ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በተገኙበት አክብረዋል::

ቅሬታ

የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም

ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ቤተል ወይራ ሰፈር አድስ አበባ ኢትዮጵያ

Useful Links